በረከት ስምዖን -የሕወሓቱ ግራዚያኒ

ተማሪዎች እንቅስቃሴ ማግስት እንደ አሸን ከፈሉት ቡድኖች መካከል አብዛኛዎቹ አማራውን ጠላት ብለው የፈረጁ ናቸው:: ከእነዚህ ቡድኖች መካከል የትግራይና የኤርትራ የፖለቲካ ቡድኖች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው:: እነዚህ ቡድኖች በማንፌስቶዎቻቸው ላይ አማራን እንደ ጠላት ሕዝብ ከመፈረጃቸው ባሻገር በቅስቀሳዎቻቸው፣ በሽለላና ዘፈኖቻቸው አማራውን የሚሰድቡና የሚያንቋሽሹ ነበሩ:: በተለይ፣ ሕወሓትና ሻዕቢያ እነሱ ከመፈጠራቸው ከ30ና 40 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን የወረረው ጣሊያን ይጠቀምበት የነበረውን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመቅረፅ፣ አማራውን ለማዳከም ገና ከጅምራቸው ሰርተዋል:: ለዚህ ስልታቸው ይጠቅም ዘንድም ለአማራው ሳይቆም ለአማራ የቆመ፣ ከአማራው አስተሳሰብ ተቃርኖም የአማራን አስተሳሰብ የያዙ ከመሰሏቸው ቡድኖች ውስጥ አንጃ በመፍጠር ሰርተዋል:: ከአንጃው ባሻገር ወደፊት ኢትዮጵያን፣ በተለይም አማራውን አዳክሞ ለመግዛት ራሱን አማራውን በሞግዚትነት የሚያስተዳድር ድርጅትና ግለሰቦችን ጠፍጥፈው ሰርተዋል:: በረከት ስምኦን አንደኛው ነው::

ጎንደር ተወልዶ ያደገው በረከት ስምኦን፣ የኢሕአፓ አባል የሆነው በ19 ዓመቱ እንደሆነ ይነገራል:: መለስ ተክሌ የሚባል የትግራይ ተወላጅ ፅንፈኛ ተማሪ መገደሉን ተከትሎ፣ ስሙን ከለገሰ ወደ መለስ እንደቀየረው መለስ ዜናዊ ሁሉ፣ በረከት ስምኦን የሚባል የኢሕአፓ ታጋይ ተገድሏል ሲባል የሰማው መብርሓቱ ገ/ሕይወት፣ ከእነ ለገሰ ዜናዊ በባሰ የኤርትራዊ ተማሪ ስም እስከ አባቱ መውረሱ ይነገራል:: ‹‹ለትግራይ እሞታለሁ›› ብሎ የተነሳው ለገሰ ዜናዊ ስሙን ለተገደለ የኦሮሞ ወይንም የአማራ ተማሪ እንዳልቀየረ ሁሉ፣ ጎንደር ተወልዶ ያደገው መብርሓቱ ገ/ሕይወትም በኢሕአፓ ዘመን በተጨፈጨፉት የጎንደር ጓደኞቹ ወይንም በሌላው አካባቢ ለተወለዱት አማራዎች ስሙን አልቀየረም፣ ለኤርትራዊው በረከት እንጅ:: ‹‹ጀግና›› የተባለን ሌላ ስም በመዋስ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብንም ጭምር ከሌሎቹ በመውሰድ የሚታወቀው በረከት ስምኦን ሕወሓት/ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላም የብአዴን ከፍተኛ አመራር ሆኖ የሕወሓትን አስተሳብ በአማራው ላይ ሲጭን የኖረ ሰው ነው::

አቶ በረከት መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ዋነኛው የመለስ ሌጋሲ አስቀጣይ፣ መለስ ዜናዊ የሚደጋግመው አብዮታዊ ዴሞክራሲ መምህር ሆኖ ቆይቷል:: አቶ በረከት ሕወሓትን በአማራው ላይ ለማንገስ የተቀመጠ እንደራሴ ስለመሆኑ ባለፉት 27 ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመው ታሪክ አስረጅ ነው:: ሆኖም፣ ይህ የእነ በረከት በአማራው ላይ የፈፀሙት ሞሶሎኒያዊ ተግባር ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የተጀመረ ሳይሆን ገና ጫካ እያሉ ያራምዱት የነበር መሆኑን የኢሕአፓና የኢሕዴን ቆይታቸውን በጨረፍታ በማየት መረዳት ይቻላል::

በኢሕአፓ ውስጥ የእነ በረከት ተልዕኮ

በኢህአፓ የ‹‹አንጃ›› ታሪክ በእነ ብርሃነ መስቀል ረዳና ጌታቸው ማሩ የሚመራው ቡድን የመጀመሪያው ተደርጎ ይወሰዳል:: ከዚህ ቀጥሎ አሲምባ ላይ ‹‹በዳግማዊ አንጃነት›› የተረሸኑት ይገኙበታል:: በሦስተኛ አንጃነት የሚቆጠረው እነ በረከት ስምኦን ይንቀሳቀሱ የነበሩበት የበለሳው ኃይል ነው:: የእነ በረከቱ አንጃ በታሪክነት የሚወስደው የኢህአፓ ታሪክ ቢኖርም ኢሕአፓን ሲያብጠለጥል በተቃራኒው ለሻዕቢያና ሕወሓት ሲዘምር የኖረ ኃይል ነው::

ኢህአፓ ውስጥ ‹‹በአንጃዎቹ›› ከተነሱት አምስት የሀሳብ ልዩነቶች መካከል ሁለቱን ብቻ ብናይ እንኳ፣ የእነ በረከቱ ኢህዴን የሚያምንባቸው አልነበሩም:: አንጀኞቹ ካነሱት ሀሳብ መካከል አንደኛው ከደርግ ጋር ፀረ ሶማሊ ግንባር መፍጠር አለብን የሚል ነበር:: ሕወሓት የሶማሊያውን ወረራ እስከ ድሬዳዋ ድረስ መንገድ መምራቱን የራሱ አንጋፋ ታጋዮችም የሚናገሩት ሀቅ ነው:: ይህን ግን የእነ በረከት ድርጅት፣ የኢሕአፓ ‹‹ሳልሳዊ አንጃ›› ነኝ እያለ፣ አንድም ቀን ተችቶት አያውቅም:: የእነ በረከቱ ኃይል አንጃ ነበርኩ የሚለው፣ ከሕወሓት ጋር የነበረውን ግንኙነት ምክንያታዊ ለማድረግ እንጅ የኢሕአፓ አንጃዎች በዋነኝነት የሚያነሱትን ጥያቄ ሲያነሳ ተደምጦ አያውቅም::

Read More

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*