በአማራ ክልል ሴቶች በአስገዳጅነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ይወስዱ እንደነበር ይፋ ሆነ

የአማራ ብሔራዊ ክልል ጤና ቢሮ ለሁሉም ለዞን ጤና ጣቢያዎች በጻፈው ደብዳቤ እናቶች በአስገዳጅ ሁኔታ ይወስዱት የነበረው የወሊድ መቆጣጠሪያ
እንዲቀር ትዕዛዝ ሰጥቷል:: የክልሉ ጤና ጥበቃ በደብዳቤው እንዳመነው፣ እስካሁን ከጠቅላላ ወሊድ መቆጣጠሪያ ከሚወስዱ እናቶች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት
የረዥም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ፣ እንዲሁም ቀሪዎቹ የአጭር ጊዜ እንዲጠቀሙ አስገዳጅ ሁኔታ እንደነበርና ይህ አሰራር ትክክል ባለመሆኑ፣ ከአሁን በኋላ እናቶች
የፈለጉትን አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ ሲል ትዕዛዝ አስተላልፏል::

የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ምክር ሲካሄድ የረዥም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያን ብቻ በማጉላትና ልዩ ትኩረት በማድረግ ሲሰራ እንደነበር ጤና ቢሮው አምኗል::
የጤና ጥበቃ ባለሙያዎች የቤተሰብ ምጣኔ፣ በተለይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ላይ በሰሩት ስራ ሲመዘኑ እንደነበር የገለፀው ጤና ቢሮው፣ የእናቶች ሞትን ለመከላከል
በሚልም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ ግፊት ሲደረግባቸው እንደነበር በደብዳቤው ይፋ አድርጓል:: በተጨማሪም፣ የጤና ባለሙያው
በሰራው የወሊድ መቆጣጠሪያ ልክ የገንዘብና የማበረታቻ ሽልማት ይሰጥ እንደነበር፣ እናቶች የወሊድ መቆጣጠርያ እንዲጠቀሙ ጥቅማጥቅምና መደለያ ሲሰጥ እንደቆየ
ደብዳቤው ፍንጭ ሰጥቷል:: ሆኖም፣ ከአሁን በኋላ ‹‹የጤና በአማራ ክልል ሴቶች በአስገዳጅነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ይወስዱ እንደነበር ይፋ ሆነ
ባለሙያው በሰራው የወሊድ መቆጣጠርያ ልክ ምንም አይነት የገንዘብም ሆነ ሌላ አይነት ማበረታቻ የማይሰጥ መሆኑን፣ እንዲሁም እናቶች የወሊድ መከላከያ
የመጠቀም ሆነ ያለመጠቀም መብት ያላቸው መሆኑ ታውቆ፣ መጠቀም ያልፈለገች እናት በጥቅማጥቅም ሆነ በሌላ መደለያ ተጠቃሚ ማድረግ የማይፈቀድ መሆኑን እንዲታወቅ፤›› ሲል አሳስቧል::

እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ እንዲጠቀሙ የሚቀሰቅሱ አካላት እናቶችን ለአንድ አይነት የወሊድ መቆጣጠርያ ዘዴ ብቻ ማስተማርና መቀስቀስ እንደማይችሉ የጠቀሰው ቢሮው፣ በተለይ የረዥም ጊዜ
የወሊድ መቆጣጠርያ በግፊት ይሰጥ እንደነበርና ይህ አሰራር እንዲቀር ትዕዛዝ ሰጥቷል:: በብዙ ጤና ጣቢያዎችም የረዥም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠርያ ይሰጥ እንደነበር
ተጠቁሟል:: ለዚህም፣ በየጣቢያዎቹ ሁሉም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መኖራቸውን መከታተል እንደሚያስፈልግ ተገልጿል:: በተጨማሪም፣ እያንዳንዱ
ጤና ጣቢያና ጤና ኬላ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የዓመታዊ እቅድ ሲሰጥ በጤና ጣቢያውና ጤና ኬላው ተጠቃሚ እናቶች ቁጥርን ያቅድ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፣
ከአሁን በኋላ እናቶች የቤተሰብ እቅድን በፍላጎት ብቻ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል::

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*