አብን የሚወገዘው ዝም ብሎ አይደለም! – (በጌታቸው ሽፈራው)

ሌላው ገና ሲንተፋተፍ ቀድሞ የመጫወቻ ካርዱን ከጠረጴዛው ላይ አነሳ። ሌላው አቀባበል ላይ ሲያተኩር አብን ማደራጀት ውስጥ ገባ! ከድግስና ምላሽ በኋላ ጠረጴዛው ላይ ካርዱ ሲታይ የለም። አብን ብድግ አድርጎታል! የአቀባበል ድግሱ ምናምን ሳያበቃ አብን 60 እና 70 ቢሮ ከፍቷል! እንግዲህ ምን ይደረግ?

አብንም ግን ይጠንቀቅ! ይህን ሁሉ እድል አግኝቶ ወደፊት ከመግፋት ውጭ ሌላ አማራጭ የለም። ከኋላ የሚጮሁበትን ትቶ የሕዝብን ጩኸት ያዳምጥ! በቃ ወደፊት ነው የሚያዋጣው!

መሪዎቹ ፎቶ መለጠፍ ይቅርባችሁ! ለሕዝብና ላገኛችሁት እድል ሲባል ራሳችሁን ደብቁት። በተለይ ፌስቡክ ላይ። የአብን አባላትም የሚሳደብ ካለ ካርዱ የተነሳበት ነውና ስቃችሁ እለፉት። ብትችሉ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ስላለው በደል ግድ እንዲለው ንገሩት! ካልሰማ ካርድ የተነሳበት ቢያለቃቅስ አይግረማችሁ።

በአሁኑ ወቅት ስለ አማራ ሕዝብ ከእናንተ የተሻለ የሚጮህ አልተገኘም። ምን አልባት ብዙዎቻችሁ ስለ ኦሮሞው ያገባኛል ባላችሁ ጊዜ “አበጀህ” ተብላችኋል። ስለ ትግራይ ሕዝብ መልካም በተናገራችው ወቅት ተሞግሳችኋል። ስለ አማራ ሕዝብ ስትናገሩ የሚወቅሳችሁና የሚጠላችሁ ካለ የእናንተ ችግር አይደለም። ስለ ኦሮሞ፣ ትግሬ……ስትናገር ወድደዋችሁ ስለ አማራው ስትናገሩ የሚጠሏችሁ ከሆነ የሚጠሉት እናንተን እንደ ግለሰብ አይደለም። አማራውን እንደ ሕዝብ ነው! ስለ ሌላ ሕዝብ ስትጮሁ ወድደዋችኋልና!

ስለሆነም ይህን ብዙው እየተነሳ የሚጠላው ሕዝብ በተጠላው መሰረት ጉዳት እንዳይደርስበት፣ እየደረሰበት ያለው ጉዳት እንዲቀንስ ቀድማችሁ ያነሳችኋትን ካርድ እጅግ በጥንቃቄ፣ በስነ ምግባር፣ በኃላፊነት ተጠቀሙባት!

መጠላታችሁን ግን አትጥሉት! ቀድማችሁ ካርድ ስለሰበሰባችሁ ነው! አይደለም በዛ ርቀት ቀድማችሁ ካርዱን ሁሉ ሰብስባችሁ ኃይሌን ፖልትይርጋት እንዴት እንደገጨው አላያችሁም እንዴ?

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*