ነጋ ማማይ ይባላል። የወልቃይት አማራ ነው።

ታህሳስ 16/2011 ዓም ወልቃይት አድረመጥ ከተማ ከምሽቱ 1:30 ወደቤቱ ሲገባ በትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ድብደባ እንደተፈፀመበት ለበረራ ገልፆአል። አቶ ነጋ ወደ ቤቱ በሚሄድበት ወቅት አንድ ልዩ ኃይል “ቁም” ብሎ ካስቆመ በኋላ ሲደበድበው “ለምን ትመታኛለህ?” ብሎ በመጠየቁ ሌሎች 3 የትግራይ ልዩ ኃይል አባላትም ድብደባ እንደፈፀሙበት ገልፆአል። አራት የልዩ ኃይል አባላቱ አስፓልት ላይ ጥለው ሲደበድቡት ሌሎችም ተጨማሪ የልዩ ኃይል አባላት ደርሰው በዱላ ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙበት ለበረራ በስልክ ገልፆአል። ከተደበደበ በኋላ ወደ እስር ቤት እንደተወሰደ የገለፀው አቶ ነጋ ምንም ያጠፋው ነገር እንደሌለና ታህሳስ 17/2011 ዓም በሰው ዋስ እንደተፈታም ተናግሯል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*