ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ለደሕንነት መስርያ ቤት ይሰራ ነበር በተባለ ግለሰብ ክስ ቀረበበት

(በረራ_ታህሳስ 18/2011 ዓ.ም)

ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ማግስት ጀምሮ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማዳከም ከብሔራዊ መረጃ ደሕንነት አገልግሎት ጋር ሲሰራ እንደነበር የሚነገርለትና የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በታሰሩበት ወቅት ድርጅቱ የተሰጠው አቶ አየለ ጫሚሶ በጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ላይ ክስ መመስረቱ ታውቋል።

መስከረም 12/2011 ዓ.ም በጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ዋና አዘጋጅነት የታተመችው ኢትዮጲስ ጋዜጣ “የአቶ አየለ ጫሚሶና የደሕንነት ግንኙነት ተጋለጠ” በሚል በሰራችው ዜና አቶ አየለ ጫሚሶ ከደሕንነት መስርያ ቤቱ ጋር የነበረውን ግንኙነት የሚታሳይ መረጃ መውጣቱ ይታወሳል። ተቃዋሚዎችን ለማዳከምና ለማጥፋት ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በሚል ድርጅት ማሕተም ከደሕንነት መስርያ ቤቱ ጋር ይሰራ እንደነበር በርከት ያሉ ደብዳቤዎች የወጡበት አቶ አየለ ጫሚሶ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን በስም ማጥፋት ወንጀል እንደከሰሰው ከፌደራል ፖሊስ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ዛሬ ታህሳስ 18/2011 ዓ.ም አቶ አየለ ጫሚሶ “ስሜ ጠፍቷል” ብሎ ላቀረበበት ክስ መልስ እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተጠርቷል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*