ብዙ ግራ የሚያጋባ ነገር አለና እንዳትደነግጡ! – (በጌታቸው ሽፈራው)

የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበረው ጥላሁን አበጀ ታህሳስ ወር 2008 ዓም ነው ወደ ኤርትራ ያቀናው። በ2009 ዓም መጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል። ዛሬ በናሁ ቲቪ ቀርቦ ታዲያ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ መሪ የተደረገላቸው የኢህአዴግ ደሕንነት እንደሆነ ገልፆአል!

በፍትሕ ሰቆቃ ዶክመንተሪ ላይ የቀረበው የንግስት ይርጋ ወንድም ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የተቀበለው ደሕንነት እንደሆነ ተናግሯል። በርካታ እስረኞች በእስር ቤት “እንትና ነው ያስያዘኝ” እያሉ የድርጅት ሰዎችን ስም ሲጠሩ ይሰማል። ግንቦት 7 ኤርትራ ከነበሩት 250 የማይበልጡ ወታደሮች በላይ ወደኤርትራ ሲያቀኑ እና ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ የተያዙ ከ300 በላይ ሰዎች እስር ቤት ውስጥ ነበሩት። ብዙዎቹ እንደጥላሁን “እንትና ነው ያስያዘኝ” ብለው ሲናገሩ የሚሰሙ ናቸው።

ያው ብዙ ግራ የሚያጋባ ነገር አለና እንዳትደነግጡ ለማለት ነው።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*